Jump to content

ታኅሣሥ ፬

ከውክፔዲያ
(ከታኅሣሥ 4 የተዛወረ)

ታኅሣሥ ፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፩ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፮፻፴፭ ዓ/ም የሆላንድ ተወላጅ መርከበኛው አቤል ታስማን የዛሬይቱን ኒውዚላንድ አገኘ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተጠነሰሰው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጀመረ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም በሲሲሊ ደሴት ላይ የተከሰተው ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ የአሥራ ስምንት ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።

፲፱፻፹፫ ዓ/ም በደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ በእሥራት ላይ ከነበሩት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር እቢሯቸው ተገናኝተው የተጠላውን የጭቆና ሥርዐት (አፓርታይድ)ን የሚወድምበትን ሁኔታ ተመካከሩ።

፲፱፻፹፱ ዓ/ም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትጸጥታ ምክር ቤት አባላት የጋናውን ተወላጅ ኮፊ አናንድን ሰባተኛው የድርጅቱ ዋና ጸሐፊነት መረጧቸው።

፲፱፻፺፮ ዓ/ም የቀድሞው የኢራክ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን ከሥልጣናቸው ሸሽተው ከተደበቁ በኋላ በአሜሪካ ሠራዊቶች በተወለዱበት ቲክሪት ከተማ አካባቢ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ።


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ