Jump to content

አበበ አረጋይ

ከውክፔዲያ

'ራስ አበበ አረጋይ' አባ ገስጥ በንጉሱ ዘመን የጦር ሚኒስቴር እንደነበሩና ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ በፈለገች ጊዜ ለ5 ዓመት በአርበኝነት የተዋጉ ጀግና ኢትዮጲያዊ ናቸው። የትውልድ ሀገራቸው ሰሜን ሸዋ ምርትና ጅሩ ወረዳ ሲሆን ልዩ ስሙ ኩሳየ(አብደላ) አካባቢ ነው።የትውልድ ዘመናቸው ፩፰፱፮ ዐ.ም ከአባታቸው ከአቶ አረጋይ በቸሬ ና ከእናታቸው ከ ወ/ሮ አስካለማርያም ጎበና ነው ።አባ ገስጥ የንጉስ ባለሟል ልጅ ነበሩ አያታቸው ራስ ጎበና ዳጨው የእምየ ምኒልክ የጦር አበጋዝ ነበሩ ።አባታቸው አቶ አረጋይ በቸሬ ደግሞ ተሟጋች ስለነበሩ ብተለያየ ጊዜ ዳኛ በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል አፈንጉስነት ማረግ ባለቤትም ነበሩ በስተ መጨረሻም የፍትህ ሚንስትር ማረግም አግኝተዋል። አባ ገስጥ በዘመኑ የነበረውን የት/ት ስርአትም ተምረዋል ከዚ በተጨማሪ በአ/አ በተቋቋመው ተፈሪ መኮንን ት/ትቤት ዘመናዊ ት/ት በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተምረዋል።ከአባታቸው ችሎትም በመዋል ልምድ ቀስመዋል ።በውትድርና ሙያም የመቶ አለቃና የሻምበልነት ማዕረግ ባለቤትም ነበሩ። በ ፩፱፪፮ ዐ.ም የባላምባራስ ማዐረግ ባለቤት በመሆን ለአ/አ ከተማ የአራዳ ዘበኛ ጥበቃ አለቃም በመሆን ሰርተዋል ። የጣልያን ጦር በወገን ጥር ላይ ብልጫ ወስዶ ውድ አ/አ እየገሰገሰ መሆኑን ሲሰሙ ሰራዊትና ቤተሰባቸውን አስከትለው ወደ ሰ/ሽዋ አቀኑ ከሳምንታት ጉዞ በሗላ ለ ሽምቅ ውጊያ ከምትመቸው ሽዋ ገቡ

ጀግነው ራስ አበበ አረጋይ ጅሩ ኩሳየ ቦታ ተወለዱ ::