አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ: República de Angolaኪኮንጎ: Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች መሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።

የአንጎላ ሪፐብሊክ
República de Angola (ፖርቱጊዝ)

የአንጎላ ሰንደቅ ዓላማ የአንጎላ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ወደፊት አንጎላ!
(ፖርቱጊዝ) Angola Avante!
የአንጎላመገኛ
የአንጎላመገኛ
አንጎላ በሰማያዊ ቀለም
ዋና ከተማ ሏንዳ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፖርቱጊዝ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
João Lourenço
ዋና ቀናት
ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፷፰
(ኖቬምበር 11, 1975 እ.ኤ.ኣ.)
 
João Lourenço የመሬት_ስፋት = 1,246,700
የሕዝብ ብዛት
የ2014 እ.ኤ.አ. ግምት
የ ቆጠራ
 
25,789,024 (50ኛ)
5,646,177
ገንዘብ ክዋንዛ
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +244
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .ao
 
ንግሥት ንዚንጋ ከሏንዳ አስተዳዳሪ ጋር የሰላም ስምምነት ስታደርግ፣ 1657 እ.ኤ.አ.

በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋል ካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፐብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።

የቅኝ ግዛት ጊዜ

ለማስተካከል

በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር።

ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት

ለማስተካከል

አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትአሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋልብራዚልደቡብ አፍሪካኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም።

የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት።

የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል።

ጦር ኃይል

ለማስተካከል

የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።

መልከዕ-ምድር

ለማስተካከል

አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች።

የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው።

የአመራር ክልሎች

ለማስተካከል
 
የአንጎላ ክልሎች በቁጥር ተሰይመው
ክልል የሕዝብ ብዛት የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) ዋና ከተማ
1. ቤንጎ 450,000 33,016 ካክሲቶ
2. ቤንጉዌላ 600,000 1,788 ቤንጉዌላ
3. ባኤ 800,000 70,314 ኩዊቶ
4. ካቢንዳ 300,000 7,283
5. ኩዋንዶ ኩባንጎ 140,000 199,049 ሜኖንጉዌ
6. ኩዋንዛ ኖርቴ 400,000 24,110 ንዳላንታንዶ
7. ኩዋንዛ ሱል 600,000 55,660 ሱምቤ
8. ኩኔኔ 200,000 87,342 ኦንዲጂቫ
9. ሁዋምቦ 1,000,000 34,270 ሁዋምቦ
10. ሁኺላ 700,000 75,002 ሉባንጎ
11. ሉዋንዳ 3,000,000 2,257 ሉዋንዳ
12. ሉንዳ ኖርቴ 103,000 103,000 ሉካፓ
13. ሉንዳ ሱል 125,000 77,637 ሳውሪሞ
14. ማላንጄ 850,000 97,602 ማላንጄ
15. ሞክሲኮ 230,000 223,023 ሉኼና
16. ናሚቤ 60,000 58,137 ናሚቤ
17. ኡዊጂ 800,000 58,698 ኡዊጂ
18. ዛየር 600,000 40,130 ምባንዛ ኮንጎ

የአንጎላ መጓጓዣዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

  • በአንድ ላይ ርዝመታቸው 2,761 ኪ.ሜ. የሆኑ ሦስት የባቡር መንገዶች
  • 76,626 ኪ.ሜ. አውራ ጎዳና ከዚህም ውስጥ 19,156 ኪ.ሜ. አስፋልት
  • 1,295 ኪ.ሜ. የውሃ መንገድ
  • ስምንት ትልቅ ወደቦች
  • 243 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ከነዚህም 32ቱ የአስፋልት መንደርደሪያ ያላቸው

አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል።

የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይና ኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው።

ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።[1]

ማመዛገቢያ

ለማስተካከል
  1. ^ (እንግሊዝኛ) ዘ ኢኮኖሚስት (The Economist). August 30, 2008 እ.ኤ.አ. ዕትም. የአሜሪካ ዕትም. ገጽ 46. Article on Angola, "marches toward riches and democracy?".