በ2017 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል
ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት 163.7 ቢሊየን ብር ገቢ ለማኘት ማቀዱን አስታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት እቅድን አስልክቶ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህወት ታምሩ በመግለጫቸውም በ2017 በጀት ዓመት ለዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ መመደቡን ጠቅሰው በቴሌኮምና ዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በዚህ መሰረት በ2017 በጀት ዓመት በቴሌኮም ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋት 1 ሺህ 298 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያ ግንባታ እንደሚያከናወን አስታውቀዋል።
4G ጋር በተያያዘ ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥር 500 ለማድረስ መታቀዱን ያስታወቁት ዋን ስራ አስፈጻሚዋ፤ 5G ኔትዎርክን ደግሞ አሁን ካለው በተጨማሪ በ15 ከተሞች እንዲጀመር ይደራል ብለዋል።
የሞባይል ኔትዎርክ አቅም ከማስፋት ጋር በተያያዘም 103.7 ሚሊየን ደንበኞች የሚያስተናድ አቅም መገንባት ማስፋፊያ እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈጻዋ አስታውቀዋል።
የደንበኞቹን ቁጥር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት የደንበኞቹ ቁጥር 78 ሚሊየን መድረሱን አስታውሰው፤ በዘንድሮ በ2017 በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።
የቴሌ በር ደንበኞች ቁጥር ጋር በተያያዘም የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥር በ2016 47.5 ሚሊየን መድረሱን ያስታወሱት ስራ አስፈጻሚዋ፤ በ2017 በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር 55 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱንም አስታውቀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ዛሬ መግለጫ እንደገለጹት በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ መታቀዱንም ገልጸዋል።
በኩባንያው በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱም የሚታወስ ሲሆን በዘንድሮ በጀት ዓመት የተያዘው እቅድ ከአምናው አፈጻጸም ጋር ሲታይ በ74 ነጥብ 7 በመቶ እድገት አለው።
በዚህ ዓመት 282 ነጥብ 85 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት መታቀዱም ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ማሻሻያ ያደርግ ይሆን?
በመግለጫው ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዝ ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ማስተካከያ ያደርጋል? የሚል ይገኝበታል?
ዋና ሥራ አሥፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በሰጡት ምላሽም፤ “ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ ምንም አይነት የታሪፍ ወይም የዋጋ ለውጥ አላደረገም” ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2018 መስረከም ወር ላይ ሰፊ የሆነ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆን ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ ማደረጉን ያስታወሱት ስራ አስፈጻሚዋ፤ ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ያደረገው የደንበኞቹንና የማህበረሰቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆን ይገባል” በሚል እንደሆነ አስታውሰዋል።
ከዚያ በኋላም ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ የታሪፍ ማሻሻዎችን ማድረጉን በማውሳት፤ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶችንም ከተመለከትን ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ነው የሚያሳየው ብለዋል።
“ዋጋ ሳታስተካክሉ እናንተስ መቀጠል ትችላላችሁ ወይ ለሚለው ጥያቄ፤ ተገቢ እና ትክክለኛ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፤ “ዘለን ታሪፉን ያለስተካከለው የደንበኞቻችንን እንዲሁም በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ እንዲረጋጋ እና ጤናማ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው”” ብለዋል።
ሁሉም ደንበኞቻችን እና ሁሉም ምርትና አገልግሎቶቻችን ላይ ዋጋ አንጨምርም፤ እንደዚሁም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባለ በወር በጣም በትንሽ በር ጥቅል የሚገዛ፤ ብዙ ለመግዛት አቅም የሌለው ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም” ሲሉም ተናግረዋል።
የዋጋ ጭማሪ ሊኖር አንደሚችልም ያነሱት ዋና ስራ እፈጻሚዋ፤ “በብዙ ብስለት፣ በብዙ አውቀት እና በብዙ ጥንቃቄ ብልሃት በተሞላበት መልኩ የት ጋር ቢጨመር ዜጎቻችን የዲጂታል አገልግሎት ጠጠቃሚ ሆነው መቀጠል እንዲችሉ ይረዳል የሚለውን ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰርተናል” ብለዋል።
ስለዚህ ይህንን መሰረት በማደረግ እና የደንበኞችን የመክፈል አቅም ታሳቢ ያደረገ መጠነኛ የሆኑ የዋጋ ጭማሪዎች ይኖረናል፤ ነገር ግን በሁሉም ደንበኞች ላይ ተፈጻሚ አይደረግም ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ ያዘጋጃቸው ሽልማቶች ምንድንናቸው?
ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው እለት በስካይ ላይ ሆቴል ባከናወንው ምርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ የኢትዮ 130 ሽልማትን ይፋ አድርጓል።
130ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ቴሌ ብርን ጨምሮ የኢትዮ ቴሌኮምን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለሚጠቀሙ ደንበኞች በመጪዎቹ ስድስት ወራት 6 የኤሌትሪክ አውቶሞቢሎች፤ 9 ባጃጅ፣ ክ160 እላይ ስማርት ስልኮችን ጨምሮ ከ260 ሺህ በላይ ፓኬጆችን ያካተተ ሽልማቶች መዘጋጀታቸው ታውቋል።