የካቲት ፳፬
Appearance
(ከየካቲት 24 የተዛወረ)
የካቲት ፳፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፸፬ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፩ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፪ ዓ/ም - እቴጌ ጣይቱ ብጡል ከሥልጣን ከመውረዳቸው ከሁለት ሣምንት በፊት፣ ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ዕለት ከሰጡት ሹመቶች አንዱ፣ የሐረርጌን ጠቅላይ ገዥነት ለደጃዝማች ተፈሪ መኮንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ነው።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - የዐቢይ ጾም ቅበላ ዕለት ዓፄ ኃይለ ሥላሴ መምህር ገብረ ጊዮርጊስን (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) እጨጌነት ሾሟቸው።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - የቤጌምድር እና የስሜን ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ደብረ ታቦር ላይ አርፈው እዚያው ተቀበሩ።
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/183838
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |