Jump to content

ከ«ፀሐይ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: lez:Рагъ
r2.7.2) (ሎሌ መጨመር: got:𐍃𐌰𐌿𐌹𐌻
መስመር፡ 105፦ መስመር፡ 105፦
[[gl:Sol]]
[[gl:Sol]]
[[gn:Kuarahy]]
[[gn:Kuarahy]]
[[got:𐍃𐌰𐌿𐌹𐌻]]
[[gu:સૂર્ય]]
[[gu:સૂર્ય]]
[[gv:Yn Ghrian]]
[[gv:Yn Ghrian]]

እትም በ02:26, 29 ሜይ 2012

ፀሓይ በውቅያኖስ ላይ ብልጭ ስትል

ፀሓይምድር ሥርዐተ-ፈለክ (planetary system) መኻል ያለች ኮከብ ናት። ምድር ሞላላ ቀለበት በሚመስል የዑደት ምሕዋር እየተጓዘች ፀሓይን ትዞራታለች። ሌሎች ሰማያዊ አካላትም፣ ፈለኮች፣ ፈለክ-አስተኔዎች (asteroids)፣ ጅራታም ከዋክብት እና ኅዋዊ ብናኞች በፀሓይ ዙሪያ ይዞራሉ።

ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር (axis) ዙሪያ እየሾረች ነው። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገው ዙረት ወቅቶች በዓመታዊ ዑደት እንዲለዋወጡ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሲኾን፣ በራሷ ዘንጎ ዙሪያ የምታደርገው ሹረት (rotation) ደግሞ በዕለታዊ ዑደት መዓልት (ቀን) እና ሌሊት ለሚያደርጉት መፈራረቅ ምክንያት ነው።

ፀሓይ ለሥርዐተ-ፈለካችን በጣም ብሩህ የኾነ ብርሃን ትሰጣለች። ያለ ፀሓይ ብርሃን ሙቀትም ኾነ ሕይወት በምድር አይኖርም ነበር። ለምሳሌ አረንጓዴ ዕፅዋት ያለ ፀሓይ ብርሃን ሊኖሩ አይችሉም፤ ለህልውናቸው የሚያስፈልጓቸውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አልሚ ምግቦች ለማስተጻመር የሚችሉት በፀሓይ ብርሃን ብቻ ነውና።

ከምድር ይልቅ ለፀሓይ ይበልጥ ቅርብ የኾኑ ፈለኮች ለከፍተኛ ጨረር እና ግለት የተጋለጡ በመኾናቸው በምድር ላይ ላለው ዐይነት ሕይወት ተስማሚ አይደሉም። ከምድር ጋር ሲነጻጸር ከፀሓይ በጣም ርቀው ያሉ ፈለኮችም ለሕይወት መኖር ምቹ ኹኔታዎች የሏቸውም፤ በቂ ብርሃን እና ሙቀት ካለማግኘታቸው የተነሣ።

የፀሓይ አካል ለፍጹም ሉል የቀረበ ቅርጽ አለው፤ ዋልታዎቿን የሚያገናኘው ዳያሜትር ከወገቧ ዳያሜትር የሚያንሰው በ10 ኪሎ ሜትር ብቻ ነውና።

ፀሓይ በልዩ ቴሌስኮፕ ስትታይ

ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን (temperature) 6,000 ኬ (ኬልቪን) ኾኖ ሳለ፣ የዳርቻ ከባቢ አየሯ ስኂን ከሚሊዮን ኬ በላይ እንዴት ሊኾን እንደቻለ አይታወቅም።

የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ (mass) ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው።

ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል (disk) መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት (supernatural phenomenon) ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ ሜክሲኮ) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን (summer solstice) ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። (በጣም ጐልተው ከሚታዩ ሜጋሊቶች ውስጥ ጥቂቱ በ ናባታ ፕላያግብጽ፣ እና በ ስቶንሄንጅእንግሊዝ፣ ውስጥ ይገኛሉ።)

ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን (ecliptic) ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የግሪክ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ።

በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ስለ ፀሓይ ሳይንሳዊ መግለጫ ለመስጠት ከቻሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ግሪካዊው ፈላስፋ አናክሳጎራስ ነበር። ፀሓይ በእሳታዊ ነበልባል የምትንቀለቀል እጅግ ግዙፍ የብረት ኳስ እንጂ የሄሊዮስ ሰረገላ እንዳልነበረች በምክንያት የተደገፈ ትንተና አቀረበ። ይህንን እንደ ኑፋቄ የተቈጠረ ሐተታ በማስተማሩም ታሰረ፤ በሞት እንዲቀጣም ተፈርዶበት ነበር፤ በፔሪክልስ አማላጅነት እንዲፈታ ተፈቀደለት እንጂ።

የባለሥልጣናት መዓት የወደቀበት ሌላው የሳይንስ ሊቅ ኒቆላዎስ ቆጰርኒቆስ ነበር። በ16ኛው ምእት ውስጥ የኖረው ቆጰርኒቆስ ምድር ፀሓይን በቀለበትማ ምሕዋር ትዞራለች እንጂ፣ ፀሓይ ምድርን አትዞርም የሚል ኀልዮ አቅርቦ ነበር። በ17ኛው ምእት ጋሊሌዮ በቴሌስኮፕ ለታገዘ የፀሓይ ጥናት ፈር-ቀዳጅ ሊቅ ኾነ። አይዛክ ኒውተን ደግሞ በፕሪዝም አማካይነት የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ አሳየ። 19ኛው ምእት ዊሊያም ኸርሽል የኢንፍራሬድ ጨረር ግኝት ባለቤት የኾነበት፣ በስፔክትሮስኮፕ ስለ ፀሓይ የሚደረገው ጥናትም እጅግ የመጠቀበት ምእት ኾነ።

የሜክሲኮ ባህላዊ ምልክት ፀሓይ

ዛሬ በብዙ አገሮች ልማድ ፀሓይ እንደ ባህላዊ ምልክት ትታያለች። ለምሳሌ በሜክሲኮ ኪነ ጥበብ አበክራ የምትታይ ሞቲፍ በመባል ትታወቃለች።

በኛ ሥርዐተ-ፀሓይ ዋናዋ ትልቅ አካል ራሷ ፀሓይ ናት። በመላው ሥርዐተ-ፀሓይ ውስጥ ከሚገኘው ክብደት 99.86% የፀሓይ ነው። ለምሳሌ ከታላቁ ፈለክ ከጁፒተር ሲነጻጸር የፀሐይ ክብደት 1000 ዕጥፍ ይበልጣል። የፀሓይ ክብደት ከምድር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል። በጣም ግዙፍ እና ከባድ የኾነችው ኮከብ ከምድር ያለችበት ርቀት በጣም የሚያስደንቅ ነው። በምድር እና በፀሓይ መካከል ያለው ርቀት የምድርን ዳያሜትር በ12,000 ጊዜ ይበልጣል። ብርሃን ይህን ርቀት ለመጓዝ 8.5 ደቂቃ ይፈጅበታል።

የፀሓይ ጭፍሮችን አካለ-መጠን ማነጻጸሪያ፦ ምድር ከግራ ሦስተኛዋ ፈለክ ናት።

መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA ak:Ewia